ኢትዮጵያ እና ጃፓን የገበያ ዕድል ስምምነት ተፈራረሙ
Back

ኢትዮጵያ እና ጃፓን የገበያ ዕድል ስምምነት ተፈራረሙ

Motri
5 min read

ኢትዮጵያ እና ጃፓን የገበያ ዕድል ፕሮቶኮል ስምምነት ተፈራረሙ።

ኢትዮጵያ እና የጃፓን የገበያ ዕድል ፕሮቶኮል ስምምነት በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ጽ/ቤት ተፈርሟል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ እንደገለጹት፤ ይህ ስምምነት የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባልነት ሂደት አካል ሲሆን፣ በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋአብ ክበበው እና በዓለም ንግድ ድርጅትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የጃፓን ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ናጋኢ ኮሱሮ ተፈርሟል።

ይህ ስምምነት እስካሁን የፈረምናቸውን የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ስምምነትን ሰባት ያደረሰ ሲሆን ከስራ ቡድን አባላት ጋር የምናደርጋቸውን ሌሎች መሰል ድርድሮችን ከማፋጠን አንጻርም አይነተኛ ተምሳሌትነት እንዳለው ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

አክለውም ከሌሎች አባላት ጋር የሚደረጉ ድርድሮችን በቅርቡ አጠናቆ ለመፈራረም በትጋት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በቅርቡ ለሚካሄደው 7ኛው የስራ ቡድን ስብሰባ የመጨረሻ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነትን እ.ኤ.አ በ2026 ለማጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቁርጠኝነት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

Ethiopian Ministry of Trade and Regional Integration

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4

Tags

#Motri#coffee