የቡና ምርት መረጃ አሰባሰብ
Back

የቡና ምርት መረጃ አሰባሰብ

ECTA
5 min read

የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የማሳ መረጃ በትክክል መሰብሰብና መያዝ ወሳኝ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ገለፀ

‎ሆሳዕና 24/04/2018

‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ቅመማ ቅመም ባላስልጣን ጋር በመተባበር በኢዩ-ካፌ በጀት ድጋፍ በEUDR ህጎችና የአርሶአደሮች ቡና ማሳ መረጃ አሰባሰብ ዙሪያ ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሶምሶን ወ/ግዮርግስ በበኩላቸው ስልጠናው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ቅመማ ቅመም ባላስልጣን ጋር በመተባበር በኢዩ-ካፌ በጀት ድጋፍ በEUDR ህጎችና የአርሶአደሮች ቡና ማሳ መረጃ አሰባሰብ ዙሪያ እየተሰጠ ነው ብለዋል ።

‎ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የሆነ እና የምርቱ መነሻና ወቅቱ የተረጋገጠ እንድሁም የተሻለ ግብይት እንድካሄድ የሚያስችል ስልጠና እንደሆነም ተናግረዋል ።

‌‎የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የማሳ መረጃ በትክክል መሰብሰብና መያዝ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል ።

‌‎የሁሉም አርሶአደሮች ከተከለ እስከ ምርት አሰባሰብ ድረስ ያለውን የቡና መረጃ ለመሰባሰብ የጋራ ግንዛቤ እንድኖር ነው ብለዋል ።

‌‎ በቡና ልማት በቴክኖሎጂ የተደገፈ መረጃ በመያዝ የግብይት ሂደቱን በማሳለጥ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ የስልጣናው ፋይዳ የጎላ እንደሆነም አንስተዋል ።

የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ሀብታሙ ታደሰ በስልጠና ወቅት እንደገለፁት ስልጠናው በቡና ምርት ግብይት ፣በመረጃ አሰባሰብና በጥራትና በአመራረት ዘይቤ ትኩረት ያደርጋል ።

‎የቡና ምርት አያያዝን በቴክኖሎጂ ከማስደገፍ አንጻር የሚስተዋሉ ውስንናቶችን ለማስቀረት በሚል በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ዶክተር ሀብታሙ ተናግረዋል ።

‎በየአከባቢው የሚገኙ የቡና አምራቾችና የማሳ ሽፋን ተለይቶ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ልዩ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም አንስተዋል ።

ሰልጣኞች እየተሰጠ ያለውን ትምህርትና ስልጠና በአግባቡ በመከታተል በየአካባቢያቸው የአርሶአደሮችን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ የድርሻቸውን እንድወጡም አስገንዝበዋል ።

‎የሀድያ ዞን ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተማም ስርጎታ እንደተናገሩት በዞኑ ከዚህ ቀደም የቡና ሽፋን 20 ሺህ ሄክተር ከነበረበት በተያየዘው በጀት ዓመት ወደ 42 ሺህ ሄክተር ማሳደግ ተችሏል ።

‎የጉራጌ ዞን ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት የኃላፊ ተወካይ አቶ ታሪኩ ወርቁ በዞኑ የቡና ሽፋን 55 ሺህ ሄክተር እንደሆነ ገልጸው ይህ ስልጣና ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል አምራቹ በቀጥታ ከገዥ ጋር እንድገነኝ እድል ይፈጥራልም ብለዋል ።

‎ከዚህ ቀደም የቡና ምርትን በተለምዶ በማምረት በአከባቢው ገበያ በማቅረብ የተጠቀሚነት ጉድለት እንደነበር ያነሱት ሀላፊዎቹ ከሽፋን ባለፈ ጥሩ ምርት የሚሰጥና በሽታን መቋቋም የሚችል የቡና ዝርያዎችን ተደራሽ በማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ።

‎የአርሶአደሮችን ተጠቀምነት ለማረጋገጥ በገበያ ትስስር ዙርያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል ።

ምንጭ ሀድያ ቴሌቪዥን

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9

Tags

#ECTA#coffee