የኢትዮጵያ የንግድ ዲፕሎማሲ ስኬት
Back

የኢትዮጵያ የንግድ ዲፕሎማሲ ስኬት

Motri
5 min read

የኢትዮጵያ የንግድ ዲፕሎማሲ ስኬት

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን ከሰባት ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ስምምነት አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ታሪካዊ ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥኑ ተጨባጭ ስኬቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ።

ሀገራችን የአባልነት ሂደቱ ወሳኝ አካል የሆነውን የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር በከፍተኛ ስኬት እያከናወነች ሲሆን፤ እስካሁን ድረስ ከሰባት የዓለም የንግድ ድርጅት የስራ ቡድን አባላት ጋር ስምምነቶችን በይፋ አጠናቃለች።

በዚህ የድርድር ሂደት ውስጥ ቻይና፣ ቱርክዬ፣ አርጀንቲና፣ ራሽያ፣ ብራዚል፣ ታይላንድ እና ጃፓን ኢትዮጵያ ስምምነቱን ያጠናቀቀችባቸው ቀዳሚ ሀገራት ናቸው።

እነዚህ ስምምነቶች ከሌሎች የሥራ ቡድን አባላት ጋር የሚደረገውን ቀሪ የድርድር ሂደት ከማፋጠን አንጻር አይነተኛ ተምሳሌትነት ያላቸው ሲሆን፤ ቀሪ ድርድሮችንም በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለመፈረም ትልቅ አቅም ይፈጥራሉ። የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ለሀገራዊ ኢኮኖሚያች ዕድገት ዘርፈ ብዙና ስትራቴጂካዊ ፋይዳዎች አሉት።

የአባልነት ሂደቱ መጠናቀቅ የሀገራችን ምርቶችና አገልግሎቶች በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ሰፊ የገበያ መዳረሻ እንዲያገኙ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። ከዚህም ባለፈ፣ ግልጽና ተገማች የሆኑ የንግድ ሕጎች እንዲሰፍኑ በማድረግ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰትን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።

ይህም ሀገራችን የጀመረችውን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ሪፎርም በማገዝ የንግድ ሥርዓቱን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ለማድረግ ሚናው የላቀ ነው።

በአሁኑ ወቅት በቅርቡ ለሚካሄደው 7ኛው የሥራ ቡድን (Working Party) ስብሰባ የመጨረሻ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ።

Gallery

Gallery image 1

Tags

#Motri#coffee