የኢትዮጵያና ጀርመን የንግድ ግንኙነት
Back

የኢትዮጵያና ጀርመን የንግድ ግንኙነት

Motri
5 min read

የኢፈድሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በኢትዮጵያና አፍሪካ ህብረት የጀርመን አምባሳደር ብርግት ኦሪ ጋር የሁለትዩሽ የንግድ ግኙነትን በተመለከት ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

ኢትዮጵያ እና ጀርመን ክፍለ ዘመንን የተሻገረ የዳበረ ድፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሃገራት መሆናቸውን ያወሱት ክቡር ሚኒስትሩ በ120 ዓመታት ውስጥ በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና በተለያዩ መስኮች ጠንካራ ትብብር መገንባት መቻላቸውን ገልጸዋል።

በሁለቱ ሃገራት መካከል ባለፉት አምስት ዓመታት በአማካይ 517 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ የንግድ ልውውጥ መደረጉንም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ወደ ጀርመን ገበያ ከሚላኩ የኢትዮጵያ ምርቶች ቡና ቀዳሚው ሲሆን በቀጣይም የወጪ ንግዳችንን ብዝሃነት ለማስፋት በትብብር ለመስራት መግባባታቸውን ክቡር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ በማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርማችን ለውጭ ባለሃብቶች በተፈጠሩ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች የጀርመን ባለሃብቶች በንቃት እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ወደ መጨረሻው ምዕራፍ በተቃረበበት በዚህ ወቅት ጀርመን በአውሮፓ ህብረት ማዕቀፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ በምትቀጥልበት ጉዳዮች ዙሪያ ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ክቡር ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8

Tags

#Motri#coffee