ክቡር አቶ ዣንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እንዲሁም የUNIDO ተወካዮች ባለስልጣን መስሪያቤቱንና የቡና ማሰልጠኛ ማዕከሉን ጎበኙ
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
ኢቡሻባ
ክቡር አቶ ዣንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ፣ የUNIDO ተወካዮች ዶ/ር ስቴቨን ካሪቦ የድርጅቱ ሰብ ሪጅናል ጽ/ቤት ዳይሬክተር እና አቶ አሰግድ የድርጅቱ ምክትል ተወካይ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ገለጻ አድራጊነት ባለስልጣን መስሪያቤቱንና የቡና ማሰልጠኛ ማዕከሉን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም ለስራና ለተገልጋይ ምቹ ሆኖ ማራኪ በሆነ መልኩ የተሠራውን አጠቃላይ የሕንጻው እድሳት የተመለከቱ ሲሆን ከዚሁ ጋ በተያያዘ የቡና ዱካ መከታተያ ክፍልን ሲጎበኙ በቴክኖሎጂ ታግዞ የሚከናወነውን የቡና ዱካ ክትትል አሠራርን እየተመለከቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
የቡና ማሰልጠኛ ማዕከሉን ሲጎበኙም በአራት የቡና ዘርፎች ማለትም በቡና ቅምሻ፣ በዘመናዊ የቡና አቆላል፣ በባሬስታ እና በኤክስፖርት ዶክመንት አያያዝ ላይ በንድፈ ሐሳብም በተግባርም የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ በተግባር እያዩ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በዚህም በእውቀትና በክህሎት የዳበረ የሰው ኃይል ለቡናው ኢንዱስትሪ በማበርከት ረገድ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተገልጿል።
Deputy Mayor of Adis Ababa City, H.E Mr. Jantirar Abay, UNIDO Representative and Director of Sub Regional Office, Dr. Stephen Kargbo, and Deputy UNIDO Representative, Mr. Asegid Adane have visited ECTA and CTC. During the visit explanation about both bodies is made by H.E. Adugna Debela(D/r), Director General of ECTA.
Visiting the building interior of ECTA, the honorable gusts observed how much the renewal of the building is attractive and convenient for work and customers. Among the work places in the building, the coffee tracing room was well visited. This time, the director General showing how the technology for coffee tracing is utilized, elaborated how it is conducted. Outsourcing, this application is made developed by the Authority itself.
As to the CTC, explanation is made about the four coffee trainings namely roasting, cupping, baresta and export documentation and how in such a way the Authority is producing skilled man power into the coffee sector.
Reported by Ashenafi Getahun








