የንግድ ሚኒስቴር የዲጂታል ስኬት
Back

የንግድ ሚኒስቴር የዲጂታል ስኬት

Motri
5 min read

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ፤ ዘመኑን የዋጀ ስኬታማ ክንውን!

(አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ንግድን ለማሳለጥ፣ የአሠራር ሂደቶችን ለማዘመንና ግልጽነትን ለማስፈን የጀመረው ዘመን-ዋጅ የዲጂታል አገልግሎት ሥርዓት በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ውስጥ ታላቅ ስኬት አስመዝግቧል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባለፉት 11 ወራት የሀገር ውስጥ ንግድን ከማሳለጥ አንጻር የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥን በማሳደግ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ 3,104,710 አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት ታቅዶ ነበር። ይሁን እንጂ በተዘረጋው የተቀናጀና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ በማሳካት 3,109,859 አገልግሎቶችን በስኬት መስጠት ተችሏል።

ይህ አጠቃላይ ክንውን የዕቅዱን 100 በመቶ ያሳካ ሲሆን፣ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ብልጫና ከፍተኛ ዕድገት ያሳየ መሆኑ ተገልጿል። ከተሰጡት አጠቃላይ የኦንላይን አገልግሎቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ፦

አዲስ የንግድ ምዝገባ 217,114 ፣

አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ 407,047 ፣

የንግድ ፈቃድ ዕድሳት 1,440,846 ፣

የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ማሻሻያ 461,619

ከዚህ ታላቅ የስኬት ቁጥር ጎን ለጎን፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሪፎርም እርምጃ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱንና የሚፈጀውን ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰ ስሆን በዚህም መሠረት ቀደም ሲል 11 መስፈርቶችን እና 32 ቀናትን ይወስድ የነበረው አሠራር፤ በአሁኑ ወቅት ወደ 3 መስፈርቶች እና 5 ቀናት ብቻ እንዲቀንስ ተደርጓል።

ይህም ለንግዱ ማኅበረሰብ ምቹና ቀልጣፋ ምኅዳርን ከመፍጠር አኳያ ትልቅ እቅስቃሴ ነው።

Gallery

Gallery image 1

Tags

#Motri#coffee