በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በተጠሪ ተቋማት የንግድ ዘርፍን ለማዘመንና አሰራሮችን ለማሻሻል የተቋቋመው የንግድ ዘርፍ ሪፎርም አብይ ኮሚቴ፤ በሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ እንዳለው መኮንን ሰብሳቢነት የሥራ አፈጻጸሙን በጥልቀት ገመገመ።
በግምገማ መድረኩ ላይ፣ በተዋረድ የሚገኙ የሪፎርም አስፈፃሚ ኮሚቴዎች በባለፉት ሳምንታት ያከናወኗቸው ዋና ዋና ተግባራት፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተገኙ ስኬቶች በዝርዝር ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የሪፎርም ስራው ዋነኛ ዓላማ የንግድ አሰራርን በማዘመን፣ የዜጎችን እንግልት በማስቀረት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠትና በንግዱ ዘርፍ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን በዘላቂነት መቅረፍ መሆኑ ተገልጿል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን በሰጡት የስራ አቅጣጫ፤ የንግድ ዘርፍ ሪፎርሙ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሽግግሩን ለማሳካት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
ኮሚቴዎቹ እስካሁን ያከናወኗቸውን አበረታች ስራዎች አጠናክረው በመቀጠል የታቀዱትን የሪፎርም ግቦች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ማሳካት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ







