የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ
Back

የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ

ECTA
5 min read

ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ጋር በተያያዘ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ

የካቲት/2018 ዓ.ም

ኢቡሻባ

ባሳለፍነው ሳምንት የኢቡሻባ ሀገራዊው የሰቪል ሰርቪስ ሪፎርም አስፈጻሚ ኮሚቴ ሪፎርሙን ከማስተግበር አንጻር ያከናወናቸውን ተግባራት ለተቋሙ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች በማቅረብ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በተቋሙ መሰብሰቢያ አዳራሽ አከናውኗል።

የሠራተኞች የስራ ሰዓት መግቢያና መውጫ ቁጥጥር ባዮሜትሪክስ ዲጂታላይዜሽን፣ የአመት እረፍት መስጫና መረጃ መያዣ ICIMIS እና ለበጀትና ንብረት አስተዳደር ጠቀሜታ ላይ የዋለው IFIMIS የተባሉ ቴክኖሎጂዎች ትስስር አጽንኦት በተሰጠበት በዚህ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ እነዚህ ሶስቱን ማቀናጀት ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ የስራ ሰዓት ቁጥጥር፣ የዓመት እረፍት አሰጣጥና የደሞዝ አከፋፈልን ማስፈንን ማስቻል እንደሆነ ተገልጿል።

በወቅቱ ከሪፎርሙ ጋር በተያያዘ የብቃትና ባህሪ ምዘና ላይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ፓወርፖይንት ቀርቧል። ምዘናዎቹ በይዘት ምን ሊመስሉ እንደሚችሉና ምን ላይ በማተኮርና በምን መልኩ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ከመድረክ ሃሳቦች ቀርበዋል።

በስተመጨረሻም የባለስልጣን መስሪያቤቱ አዲስ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በመምረጥ የመድረኩ ፍጻሜ ሆኗል።

አሰራርን ዲጂታላይዝ ከማድረግ አንጻር እንደሀገር ከሚተገበሩት ባሻገር ቀደም ብሎም ባለስልጣን መስሪያቤቱ ቀድሞ ሚምስ (MIMS) ኋላ ላይ አሻሽሎት ኢሲቲ ኤም ኤስ (ECTMS) የተሰኘ የቡና ዱካ መከታተያ ቴክኖሎጂዎችን እና የመሳሰሉትን በማስበልጸግ ተግባራዊ እያደረገ መቆየቱ ይታወሳል

አሸናፊ ጌታሁን እንደዘገበው

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8

Tags

#ECTA#coffee