የዋና ዳይሬክተሩ ከቻይና ልዑካን ጋር ያደረጉት ውይይት
Back

የዋና ዳይሬክተሩ ከቻይና ልዑካን ጋር ያደረጉት ውይይት

ECTA
5 min read

ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ የቻይና ልዑካንን ተቀብለው አነጋገሩ!!

ሚያዝያ 14/2018፡ አዲስ አበባ

ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በዛሬው እለት ከቻይና HONGQIAO አለማቀፍ ኢኮኖሚክ ፎረም የመጡ እንግዶችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ በቅርቡ በቻይና በሚካሄደው ኢንተርናሽናል ኢምፖርት ኤክስፖርት ኤክስፖ የዘርፉ ተዋናዮች ተሳታፊ በሚሆኑበት እና ምርቶቻቸውን ማስተዋወቅ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ አገራችን ወደ ቻይና እየላከችው ካለው የቡና ምርት ጋር ተያይዞ ከአመት ወደ አመት እያታየ ያለውን ከፍተኛ እድገት እንዲሁም ቀጣይ በሚጠበቁ ሁኔታዎች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ መንግስት ለውጭ ባለሀብቶች በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች እንዲሳተፉ የሰጠውን እድል ለመጠቀም የተለያዩ የቻይና ኩባንያዎች በዘርፉ ለመሳተፍ ወደ አገራችን እየመጡ መሆናቸውን የጠቆሙት ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ወደፊት ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በቡናው ዘርፍ ጋር ያላትን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ለሚደረገው ጥረት በመንግስት አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2

Tags

#ECTA#coffee